አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ ቀን መካ ውስጥ እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራን በርሱ ጀልባዎቻችን ይለቀለቃሉ፣ ቆዳችንን እንቀባበታለን፣ ሰዎ…

