ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ። በሰዎች ላይ የተሾመ መሪ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ወንድ በቤተሰቡ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ሴት ልጅ በቧሏ ቤትና በልጆቹ ላ…

