እንዲያ ከሆነ እኔን አታስመስክረኝ! እኔ በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ።
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዺየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የኑዕማን እናት ቢንት ረዋሓ ለልጇ ኑዕማን ከገንዘቡ የተወሰነ ስጦታ እንዲሰጠው አባቱን ጠየቀችው። አንድ ዓመት ከዘገየ በኋላ ስጦታውን መስጠቱ ላይ ተስማማ። እርሷም "ለልጄ በምትሰጠው ስጦታ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስክታስመሰክር ድረስ አልደሰትም።" አለች። እኔም ህፃን ነበርኩኝና…

