‹‹ከትንሳኤ ቀን ችግሮች አላህ እንዲገላግለው ያስደሰተው ሰው ለችግርተኛ ፋታ ይስጥ ወይም ከርሱ ያቅልልለት።
ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አቡ ቀታዳህ አንድ ተበዳሪውን ሲፈልገው ከርሱ ተሸሸገ። ከዚያም አገኘው። ተበዳሪውም "እኔ ችግርተኛ ነኝ።" አለው። እርሱም "ወላሂ በል!" አለው። ተበዳሪውም "ወሏሂ!" አለ። አቡቀታዳም እንዲህ አለ: "እኔ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:‐ ‹‹…

