ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር የሚመልሱት።
ከአቢ ዐብደላህ አልጀደሊይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአማኞች እናት ዓኢሻን (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ጠየቅኳት። እርሷም እንዲህ አለች: "ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ…

