የምትችሉትን ስራ ያዙ። በአላህ እምላለሁ። (መስራት) እስክትሰለቹ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመስጠት) አይሰለችም።" አሉ።
የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከዓኢሻ ጋር ሆነው ሳሉ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ቢን ሐቢብ ቢን አሰድ ቢን ዐብዲልዑዛ በዓኢሻ በኩል አለፈች። እኔም "ይህቺ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ናት። እርሷም ሌሊት እንደማትተኛ ገለፁልኝ።" አልኳቸው…

