እኔ በሰማይ ላለው (ለአላህ) ታማኝ ሆኜ፤ የሰማይ ወሬም ጠዋትና ማታ እየመጣልኝ አታምኑኝምን?!።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከየመን በቀረዝ ቅጠል ታሽቶ በተዘጋጀ ከረጢት ከማዕድኑ አፈር ያልጠራን የወርቅ ቁርጥራጭ ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላከ። እሳቸውም ለአራት ሰዎች አከፋፈሉት።…

