HadeethEnc · 1.23.0
አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።"
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም ውዱእ አድርጎ ኹፎቹን ከለበሰ በኋላ ዉዱኡን አፍርሶ ዉዱእ ማድረግ ከፈለገ ኹፎቹ ላይ ማበስ እንደሚችል፣ ለተገደቡ ጊዜያትም ሳያወልቃቸው እነርሱን እንደለበሰ መስገድ እንደሚችል ገለፁ። ጀናባ ካጋጠመው ግን ኹፉን አውልቆ የመታጠብ ግዴታ አለበት።
03
Benefits
ኹፎቹ የተሟላ ዉዱእ ካደረጉ በኋላ የተለበሱ ካልሆኑ በቀር በነርሱ ላይ ማበስ አይፈቀድም።
የማበሻ ጊዜ ገደብ ሀገሩ ለተቀመጠ ሰው አንድ ቀን ከነሌሊቱ ሲሆን ጉዞ ላይ ላለ ሰው ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ነው።
በኹፎች ላይ ማበስ የሚፈቀደው ዉዱእ የሚያስደርግ ነገር ሲያጋጥመን እንጂ ገላ የሚያስታጥብ ነገር ሲያጋጥም አይደለም። ገላ የሚያስታጥብ ነገር ሲያጋጥም ማበስ አይፈቀድም። ይልቁንም የግድ ሁለቱን ኹፎች ማውለቅና እግሮቹንም ማጠብ ይኖርበታል።
ኹፎችን፣ ጫማዎችንና የመሳሰሉትን ለብሶ መስገድ የሁዶችን ለመቃረን ሲባል ይወደዳል። ይህ ግን ንፁህ የሆነ ጊዜ፣ ሰጋጆችንና መስጂድን የሚያውክ ነገር የሌለው ጊዜ ነው። ለምሳሌ መስጂዱ ምንጣፍ የተነጠፈበት ጊዜ ጫማውን ለብሶ አይሰግድም።
በሁለቱ ኹፎች ላይ ማበስ መፈቀዱ በውስጡ ለዚህ ኡመት ማግራራትና ማቅለልን ይዟል።

Attribution
[ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares