HadeethEnc · 1.23.0
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ። ከርሳቸው ገሸሽ ስል "ቅረብ" አሉኝ። እግራቸው አጠገብ እስከምቆም ድረስ ቀረብኩ። ዉዱእ አደረጉና በኹፋቸው ላይ አበሱ።
02
Explanation
ሑዘይፋ ቢን አልየማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መሽናት ፈለጉና የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ገቡ። የአብዛኛው ጊዜ ልማዳቸው ተቀምጦ መሽናት ቢሆንም ቆመው ሸኑ።
ሑዘይፋም ከርሳቸው ራቅ አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ቀረብ በል!" አሉት። ሑዘይፋም በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከእይታ ሊጋርዳቸው ከኋላቸው ተረከዛቸው አጠገብ እስኪቆም ድረስ ቀረባቸው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው ዉዱእ አደረጉ። እግራቸውን የሚታጠቡበት ቦታ ላይ ሲደርሱም ኹፋቸውን ሳያወልቁ በላዩ ላይ በማበስ ብቻ ተብቃቁ። ኹፍ ማለት ከቀጭን ቆዳ ወይም ከመሳሰሉት የሚሰራ እግር ላይ የሚጠለቅና እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ የሚለበስ ካልሲ ነው።

03
Benefits
በኹፎች ላይ ማበስ መደንገጉን እንረዳለን።
ቆሞ መሽናት መፈቀዱን እንረዳለን። ነገር ግን ሽንቱ ምንም አለመንካቱ መስፈርት ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቆሻሻ መጣያን የመምረጣቸው ምክንያት ይህ ስፍራ ለስላሳና በአብዛኛው ጊዜ ሽንቱ ወደሚሸናው አካል ስለማይረጭ ነው።
ቆሞ መሽናት መፈቀዱን እንረዳለን። ነገር ግን ሽንቱ ምንም አለመንካቱ መስፈርት ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቆሻሻ መጣያን የመምረጣቸው ምክንያት ይህ ስፍራ ለስላሳና በአብዛኛው ጊዜ ሽንቱ ወደሚሸናው አካል ስለማይረጭ ነው።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares