የትንሳኤ ቀን ከእሳት ነዋሪዎች እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት ለሚቀጣው አላህ እንዲህ ይለዋል: "ምድር ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ቢኖርህ ያንን ነገር ፍዳ ታደርገዋለህን?" እርሱም: "አዎን" ይላል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ «የትንሳኤ ቀን ከእሳት ነዋሪዎች እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት ለሚቀጣው አላህ እንዲህ ይለዋል: "ምድር ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ቢኖርህ ያንን ነገር ፍዳ ታደርገዋለህን?" እርሱም: "አዎን" ይላል። አላህም "በአደም ጀርባ እያለህ ካንተ ከዚህም ያነሰ ነገር ነበር የፈለግኩት: በኔ አንዳችንም አታጋራ ነበር ያልኩህ። አንተ ግን በኔ ማጋራትን እንጂ ሌላውን ነገር እምቢ አልክ።"»
Explanation
Benefits
በአላህ የማጋራት አደገኝነትንና ፍፃሜውን እንረዳለን።
አላህ የአደም ልጆች በአባታቸው አደም ጀርባ ላይ ሳሉ እንዳያጋሩ ቃል ኪዳን ከነርሱ መውሰዱን እንረዳለን።
ከሺርክ መጠንቀቅ እንደሚገባና ከሀዲ ለሆነ ሰው የትንሳኤ ቀን ዱንያ ባጠቃላይ ተሰብስባ አንዳችም እንደማትጠቅመው እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

