HadeethEnc · 1.23.0
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ስነምግባር ቁርአን ነበር።' አለችኝ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ሰዕድ ቢን ሂሻም ቢን ዓሚር እናታችን ዓኢሻህ ዘንድ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- የገባ ወቅት እንዲህ አለ: "የሙእሚኖች እናት ሆይ! ስለአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ንገሪኝ! እሷም 'ቁርአን አትቀራምን?' አለችኝ። እኔም 'እንዴታ!' አልኩኝ። እሷም ' የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ስነምግባር ቁርአን ነበር።' አለችኝ።"
02
Explanation
የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ስለነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ተጠየቀች። ጠያቂውን ሁሉንም ምሉዕ ባህሪያት ወደ ሰበሰበው ወደ ተከበረው ቁርአን በመመለስ ጠቅላይ በሆነ ንግግር መለሰችለት። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁርአናዊውን ስነምግባር የተላበሱ ፤ ቁርአን ያዘዘውን ይፈፅሙ፣ ቁርአን የከለከለውን ደግሞ ይርቁ እንደነበር፤ የሳቸው ስነምግባር በቁርአን መስራት ፣ ድንበሩ ላይ መቆም፣ የቁርአንን አዳብ መላበስ ፣ ምሳሌዎቹንና ታሪኮቹን ማስተንተን ነበር ብላ መለሰችለት።
03
Benefits
ነቢዩ ቁርአናዊ ስነምግባር በመላበሳቸው ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አርአያ በማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መሞገሱ። የሳቸው ስነምግባር ከወሕይ ምንጭ የተቀዳ ነውና።
ቁርአን ለሁሉም የተከበሩ ስነምግባሮች ምንጭ መሆኑን እንረዳለን።
ስነምግባር በኢስላም ሁሉንም የሃይማኖቱን ክፍሎች ያጠቃልላል፤ ይህም ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መሞገሱ። የሳቸው ስነምግባር ከወሕይ ምንጭ የተቀዳ ነውና።
ቁርአን ለሁሉም የተከበሩ ስነምግባሮች ምንጭ መሆኑን እንረዳለን።
ስነምግባር በኢስላም ሁሉንም የሃይማኖቱን ክፍሎች ያጠቃልላል፤ ይህም ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው።
Attribution
[ሙስሊም ረጅሙ የሐዲሥ ጥቅል ውስጥ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

