HadeethEnc · 1.23.0
ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "ዑሥማን ቢን ዐፋን (የነቢዩን) መስጂድ መገንባት ፈለጉ። ይህንንም ሰዎች ጠሉ። ባለበት እንዲተወውም ፈለጉ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።"
02
Explanation
ዑሥማን ቢን ዐፋን አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂዱ መጀመሪያ ከነበረበት ባማረ መልኩ አድሶ መገንባት ፈለጉ። ሰዎችም መስጂዱ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመን ከነበረበት ሁኔታ ስለሚለወጥ ይህንን የዑሥማን ሀሳብ ጠሉ። የመስጂዱ ግድግዳ በጡብ የተገነባ ሲሆን ጣሪያው በዘንባባ ቅጠል ነበር የተሰራው። ዑሥማን ግን በድንጋይና በጀሶ ነበር መገንባት የፈለጉት። በዚህ ጊዜ ዑሥማን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ለይዩልኝና ይስሙልኝ ሳይሆን የአላህን ውዴታ ፈልጎ መስጂድ የገነባ አላህ በስራው አይነት የበለጠ ምንዳ ይመነዳዋል። ይህም ምንዳ በገነባው ቤት አምሳያ አሏህም ለርሱ ጀነት ውስጥ የሚገነባለት መሆኑ ነው።" ሲሉ መስማታቸውን ነገሯቸው።
03
Benefits
መስጂዶችን በመገንባት ላይ መነሳሳቱና የዚህንም ትሩፋት እንረዳለን።
መስጂድን ማስፋትና ማደስ የመገንባት ትሩፋት ውስጥ ይካተታል።
በሁሉም ስራዎች ስራን ለአላህ ማጥራት አንገብጋቢነቱን እንረዳለን።
መስጂድን ማስፋትና ማደስ የመገንባት ትሩፋት ውስጥ ይካተታል።
በሁሉም ስራዎች ስራን ለአላህ ማጥራት አንገብጋቢነቱን እንረዳለን።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

