ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "እኔ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድን ሐዲሥ የሰማሁ ጊዜ አላህ በዛ ሐዲሥ በሻው መንገድ የሚጠቅመኝ ሰው ነበርኩ፤ ከሶሐቦቻቸው መካከል አንድ ሰው ሐዲሥ የነገረኝ ጊዜ ታዲያ አስምለዋለሁ። ከማለልኝ አምነዋለሁ። አቡበከር ለኔ አንድ ሐዲሥ ነግሮኛል። አቡበከር የነገረኝም እውነት ነበር። አቡበከር እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።› ቀጥለውም ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት} [ኣሊ ዒምራን:135] '"
Explanation
Benefits
የአላህ ምህረት ሰፊ መሆኑንና፤ ተውበትና ምህረት ሲጠየቅ እንደሚቀበል እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

