ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ዚያድ ቢን ለቢድ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።
Explanation
Benefits
የዕውቀት መጥፋት በተለያየ መልኩ ይከሰታል። ከነሱም ውስጥ: - የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሞት፣ የዑለሞች ሞት፣ በዕውቀት መስራት መተው ይጠቀሳሉ።
ከሰዓቲቱ ምልክቶች ውስጥ የዕውቀት መጥፋትና በሱ አለመስራት ይጠቀሳል።
በዕውቀት መሥራት ላይ መነሳሳቱ እሱ ነውና ዋናው የተፈለገው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

