የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰማ: "የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል።" ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ "ቀልቦችን አዘዋዋሪ የሆንከው አላህ ሆይ! ቀልባችንን በአምልኮህ ላይ አዙረው።"
Explanation
Benefits
አንድ ሙስሊም በእውነትና ቅናቻ ላይ ጌታው እንዲያፀናው አዘውትሮ መጠየቅ ይገባዋል።
አጋር በሌለው በአላህ ብቻ ቀልብን ማንጠልጠልና እርሱን ብቻ መፍራት እንደሚገባ እንረዳለን።
አጁርሪይ እንዲህ ብለዋል: "የሐቅ ባለቤቶች አላህ ነፍሱን በገለፀበት ነገር፣ መልክተኛው (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህን በገለፁት ነገርና ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አላህን በገለፁት ነገር ይገልፁታል።" ይህ ሐቁን የተከተሉና አዲስ ነገር ያልፈጠሩ ዑለማዎች መንገድ ነው።" (ንግግራቸው ተጠናቀቀ)። አህሉ ሱናዎች አላህ ለነፍሱ ያፀደቀውን ስሞችና ባህሪያት ሳያጣምሙ፣ ትርጉም አልባ ሳያደርጉ፣ አኳኋኑን ሳይገልፁና ሳያመሳስሉ ለአላህ ያፀድቃሉ። አላህ ከራሱ ላይ ውድቅ ያደረገውንም ነገር ውድቅ ያደርጋሉ። ማፅደቅም ሆነ ውድቅ ማድረግ ላልመጣበት ጉዳይም ዝም ይላሉ። አላህ እንዲህ ብሏል: {የሚመስለው ምንም ነገር የለም። እርሱም ሰሚው ተመልካች ነው።}"
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

