HadeethEnc · 1.23.0
ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።"
02
Explanation
የነርሱ መለዮ የሆነን እምነት ወይም አምልኮ ወይም ተለምዷዊ ነገርን በማድረግ ከከሀዲያን ወይም ከአመፀኞች ወይም ከደጋግ ህዝቦችም ጋር የተመሳሰለ ሰው ከነርሱ እንደሚመደብ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ምክንያቱም በውጫዊ ማንነት ከነርሱ ጋር መመሳሰል በውስጣዊ ማንነት ከነርሱ ጋር ወደ መመሳሰል ያደርሳልና። ከሆኑ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በነሱ የመደነቅ ውጤት መሆኑ ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው። ቀስ በቀስም እነሱን ወደመውደድ ፣ ወደማላቅ፣ ወደነርሱ ጥገኛ ወደመሆን ያደርሳል። ይህም አላህ ይጠብቀንና ሰውዬውን በውስጣዊ አመለካከቱና አምልኮው ሳይቀር ከነርሱ ጋር ወደመመሳሰል ይጎትተዋል።
03
Benefits
ከከሀዲያንና አመፀኛ ህዝቦች ጋር መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።
ከደጋጎች ጋር መመሳሰልና እነሱን መከተል መበረታታቱን እንረዳለን።
በውጫዊ ማንነት መመሳሰል በውስጥ መውደድን እንደሚያወርስ እንረዳለን።
ሰውዬው በተመሳሰለው ልክና አይነት ወንጀልና ዛቻ እንደሚያጋጥመው እንረዳለን።
ከከሀዲያን ጋር እነሱ የተለዩበት በሆኑ እምነታቸውና ተለምዷቸው መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን። ይህ ባልሆነበት የተለያዩ ሙያዎችን መማርና የመሳሰሉት ግን ክልከላው ውስጥ አይካተትም።

Attribution
[አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares