‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ ነፃ ያወጡት ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ምክንያት ጀነት እንድገባ የሚያደርገኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።»
Explanation
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጠያቂው እንዲህ አሉት: ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማብዛትን አዘውትር! አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም ቢምርህ እንጂ አንድም ሱጁድ ለአላህ አትወርድም።
Benefits
የሶሐቦች ግንዛቤና እውቀት መገለፁ። ይህም ጀነት ከአላህ እዝነት በኋላ በስራ ካልሆነ በቀር እንደማትገኝ ማወቃቸው ነው።
ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማድረግ ደረጃን ከፍ ለማድረግና ወንጀሎችን ለማስማር ትልቁ ምክንያት ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

