HadeethEnc · 1.23.0
'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰሙ፡ "በካዕባ ይሁንብኝ በፍፁም!" ኢብኑ ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲሁ አሉ፡ "ከአሏህ ውጭ ባለ አካል አይማልም! ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁና 'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"
02
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአሏህ ወይም በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር ከዛ ውጪ በሆነ መሀላ የማለ ሰው በአላህ ክዷል ወይም አጋርቷል ብለው ተናገሩ። ምክንያቱም በአንድ አካል መማል እሱን ማላቃችንን ያስፈርዳል፤ በእውነቱ ልቅና ደግሞ የሚገባው ለአሏህ ብቻ ነው። ስለዚህም በሱ ወይም ከስምና ባህሪዎቹ መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር አይማልም። ይህ መሀላ ከትንሹ ሽርክ የሚመደብ ነው። ይሁን እንጂ የማለው ሰው የማለበትን አካል እንደ አሏህ ወይም ከዛም በላይ አልቆት ከሆነ ግን መሃላው ትልቁ ሽርክ ይሆናል።
03
Benefits
በመሀላ ማላቅ ጥራት የተገባው የአሏህ ሐቅ ነው። በመሆኑም በአላህ ፣ በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማልም።
ሰሓቦች በመልካም ለማዘዝ እና ከመጥፎ ለመከልከል የነበራቸውን ጉጉት ያሳያል፤ በተለይም ጥፋቱ ሽርክን ወይም ክህደትን የሚመለከት ሲሆን የበለጠ ጉጉት አላቸው።
ሰሓቦች በመልካም ለማዘዝ እና ከመጥፎ ለመከልከል የነበራቸውን ጉጉት ያሳያል፤ በተለይም ጥፋቱ ሽርክን ወይም ክህደትን የሚመለከት ሲሆን የበለጠ ጉጉት አላቸው።
Attribution
[አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

