افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم. افتتاح البرنامج الدعوي السبت القادم، ٩ / ٣ / ١٤٤٨هـ بعد صلاة الفجر مباشرة مسجد محمد بن إبراهيم، الجامعة الإسلامية بالمدينة المنورة فضيلة الشيخ د. هيثم بن محمد سرحان دورة اليوم الواحد، وختم كتاب كل سبت بإذن الله حياكم الله ونفع بكم.
#3138[ሶሒሕ ነው።]
HadeethEnc · 1.23.0

ሰውዬው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሀዲ ሆኖ የሚያመሽበት፤ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሀዲ ሆኖ የሚያነጋበት፤ እምነቱንም በአለማዊ ሸቀጥ እስከመሸጥ የሚያደርሱ የድቅድቅ ጨለማ ቁራጭ የመሰሉ ፈተናዎች ከመምጣታቸው በፊት በመልካም ስራ ተቻኮሉ።

Available translations

Choose an available translation of this Hadeeth

01

Hadeeth text

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሀዲ ሆኖ የሚያመሽበት፤ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሀዲ ሆኖ የሚያነጋበት፤ እምነቱንም በአለማዊ ሸቀጥ እስከመሸጥ የሚያደርሱ የድቅድቅ ጨለማ ቁራጭ የመሰሉ ፈተናዎች ከመምጣታቸው በፊት በመልካም ስራ ተቻኮሉ።"
02

Explanation

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልካም ስራ ከመፈፀም የሚከለክሉና የሚያቅቡ ፈተናና ማምታቻዎች መጥተው መልካም ስራ መስራት ከባድ ከመሆኑ በፊት አማኞች ወደ መልካም ስራ እንዲቻኮሉና እንዲያበዙ አነሳሱ። ይህም ፈተና እንደ ሌሊት ቁራጭ ድቅድቅ ጨለማ በመሆኑ እውነቱ ከሀሰት ጋር ተደበላልቆ ለሰዎች እውነትን ከውሸት መለየት የሚከብድበት ፈተና ነው። ከፈተናዋ መክበድ የተነሳ ሰውዬው አማኝ ሆኖ አንግቶ ከሀዲ ሆኖ እስኪያመሽ፤ አማኝ ሆኖ አምሽቶ ከሀዲ ሆኖ እስኪያነጋና ጠፊ በሆነው አለማዊ ጥቅም ሃይማኖቱን እስኪተው ድረስ ሰዎች ይዋልላሉ።
03

Benefits

ሃይማኖቱን በአግባቡ ከመተግበር የሚከለክሉ ግርዶሾች ከመምጣታቸው በፊት ሃይማኖትን አጥብቆ መያዝና ወደ መልካም ስራ መቻኮል ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
በመጨረሻው ዘመን አጥማሚ ፈተናዎች ተከታትለው እንደሚመጡ መጠቆማቸው። ይህም አንድ ፈተና በተወገደች ቁጥር ሌላ ፈተና ይከተላታል።
የሰው ልጅ እምነት በደከመ ጊዜና ለገንዘብም ሆነ ለሌላ ዓለማዊ ጉዳዮች እምነቱን አሳልፎ ከሰጠ ይህ ከእምነቱ ለመጣመም፣ እምነቱን ለመተዉና ከፈተና ጋር አብሮ ለመነዳቱ ሰበብ ይሆንበታል።
እዚህ ሐዲሥ ውስጥ መልካም ስራዎች ከፈተና ለመዳን ምክንያት እንደሆኑ ይጠቁማል።
ፈተናዎች በሁለት ይከፈላሉ:- አንዱ የማምታቻ (የሹበሃ) ፈተናዎች ሲሆን መፍትሄውም ዕውቀት ነው። ሌላው ደግሞ የዝንባሌ/ ፍላጎት (የሸህዋ) ፈተናዎች ሲሆን መፍትሄውም ኢማንና ትእግስት ነው።
ይህ ሐዲሥ ስራው ያነሰ ሰው ፈተና ወደርሱ በፍጥነት እንደሚመጣና ስራው የበዛ ሰው ደግሞ በሰራው ስራ (ተመፃድቆ) መሸወድ እንደማይገባውና ይልቁንም ጨምሮ ማብዛት እንዳለበት ይጠቁማል።

Attribution

[ሙስሊም ዘግበውታል።]

Categories

Share

Share hadeeth

Sharing options · 0 Total shares

Share

← Back to encyclopedia
Shopping Basket

Loading...