HadeethEnc · 1.23.0
የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የጁሙዐ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ሳለ ለባልደረባህ 'ዝም በል!' ካልከው በርግጥም ውድቅ ንግግርን ተናግረሀል።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጁሙዓ ኹጥባ ላይ የተሳተፈ ሰው ሊያሟላቸው ከሚገባ ግዴታ ስርዐቶች መካከል ተግሳፁን ሊያስተነትን ዘንድ ኹጥባ አድራጊውን በጥሞና ማዳመጥ እንደሚገባ ግልፅ አደረጉ። ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለሌላ ሰው "ዝም በል!" "አዳምጥ!" እንደማለት ትንሽ ነገር እንኳ ያወራ ሰውም ቢሆን የጁመዐ ሶላት ትሩፋት እንዳመለጠው ተናገሩ።
03
Benefits
ኹጥባ በሚደመጥበት ወቅት መጥፎን ማውገዝ ወይም ሰላምታን መመለስና ያስነጠሰን "የርሐሙከላህ" ማለትን እንኳ ቢሆን ማንኛውም ንግግር መናገር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ኢማሙን የሚያዋራ ወይም ኢማሙ የሚያወራው ሰው እዚህ ክልከላ ውስጥ አይካተትም።
አስፈላጊ ከሆነ በሁለቱ ኹጥባዎች መካከል ማውራት ይፈቀዳል።
ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተወሱ ድምፅህን ቀንሰህ በሳቸው ላይ ሶላትና ሰላም ታወርዳለህ። ልክ እንደዚሁ ዱዓ ሲደረግም በዝግታ (ድምፅህን ቀንሰህ) አሚን ትላለህ።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares