HadeethEnc · 1.23.0
(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "(የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙአዚንን በምንሰማ ጊዜ ለርሱ ጥሪ መልስ በመስጠት ላይ አነሳሱ (አበረታቱ)። ምላሹም በየአንዳንዱ አረፍተ ነገር ሙአዚኑ የሚለውን በማለት ነው። ተክቢራው በሚያደርግ ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ ተክቢራ እናደርጋለን፣ ሁለቱን የምስክር ቃላት (ሸሀደተይንን) በሚል ጊዜ እኛም ከርሱ በኋላ እንላለን፣ (ሐይየ ዐለስ-ሶላህና ሐይየ ዐለል ፈላሕ) የሚሉት ሁለቱ አረፍተ ነገሮች ግን ይለያሉ። ከነርሱ በኃላ የምንለው "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" (ብልሃትም ሆነ ኃይል ከአላህ ውጪ የለም) ነውና።
03
Benefits
የሐዲሱ ጥቅል መልዕክት ስለሚያስፈርድ አዛን ባዮች ከበዙ የመጀመሪያው ሙአዚን አዛን ከተጠናቀቀ በኋላ የሁለተኛውንም ሙአዚን አዛን ተከትሎ ለጥሪው መልስ ይሰጣል።
መፀዳጃ ቤት ውስጥ ወይም እየተፀዳዳ እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን ለሙአዚን ጥሪ መልስ መሰጠት አለበት።
መፀዳጃ ቤት ውስጥ ወይም እየተፀዳዳ እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆን ለሙአዚን ጥሪ መልስ መሰጠት አለበት።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

