አንዳችሁ ከሶስት ድንጋይ ባነሰ ኢስቲንጃእ እንዳያደርግ (እንዳያጥራራ)።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከሰልማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አጋርያኖች ለኛ እንዲህ አሉን: "እኔ እንደማየው ባልደረባችሁ እንዴት እንደምትፀዳዱ ሳይቀር ያስተምራችኋል አይደል?" እኔም እንዲህ በማለት መለስኩላቸው አዎ እርሳቸው እያንዳንዳችን በቀኝ እጁ ከመጥራራት (ኢስቲንጃእ ከማድረግ) ወይም ወደ ቂብላ አቅጣጫ ዞሮ ከመፀዳዳት ከልክለውናል። በፍግና በአጥንት ከመፀዳዳት (ኢስቲንጃእ ከማድረግም) ከልክለውናል። እንዲህም ብለውናል "አንዳችሁ ከሶስት ድንጋይ ባነሰ ኢስቲንጃእ እንዳያደርግ (እንዳያጥራራ)።"»
Explanation
Benefits
የተወሰኑ የመፀዳዳትና የኢስቲንጃእ አዳቦች ተገልፀዋል።
በመሽናት ወይም ሰገራን በማውጣት ወቅት ወደ ቂብላ መዞር ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ይህም "ከለከሉን" ከሚለው ቃል ነው የምንረዳው። ክልከላ በመሰረቱ ሐራምነትን ነው የሚጠቁመውና።
ቀኝ እጅን ለማክበር በቀኝ እጅ ኢስቲንጃእም (በውሃ መታጠብ) ሆነ ወይም ማደራረቅ መከልከሉን እንረዳለን።
ቀኝ እጅ ከግራ እጅ እንደሚበልጥ እንረዳለን። ይኸውም ግራ እጅ ነጃሳንና ቆሻሻን ለማስወገድ ነው የምንጠቀምበት። ቀኝ እጅን ግን ከዛ ውጪ ላለ ነው የምንጠቀምበት።
ነጃሳን አነሰችም በዛችም በውሃ ወይም በድንጋይ ማስወገድ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ከሶስት ድንጋይ ባነሰ ማደራረቅ መከልከሉን እንረዳለን። ይኸውም በአብዛኛው ከሶስት ድንጋይ ያነሰ ስለማያጠራ ነው።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ድንጋይን የጠቀሱት በአብዛኛው የሚጠቀሙት እርሱን ስለሆነ እንጂ የታለመውን ማጥራትና ማፅዳት ሊያስገኝልን የሚችል ነገር ሁሉ መጠቀም ይፈቀዳል። እንዲህ የሆነ ነገር ደግሞ ከርሱ ውጪ ባለ በሌላ ነገር አይፈቀድም የሚልን አያስገነዝብም።
ማደራረቅን በጎዶሎ ቁጥር ማጠናቀቅ እንደሚወደድ እንረዳለን። በአራት ድንጋይ ከጠራለት አምስተኛን መጨመሩ ይወደዳል። ይህም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - (ያደራረቀ ሰው ማደራረቁን በጎዶሎ ቁጥር ያጠናቅቅ) ስላሉ ነው።
በፍግ ኢስቲጅማር ማድረግ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ወይ ነጃሳ ስለሆነ ነው ወይም የጂን እንስሶች ቀለብ ስለሆነ ነው።
በአጥንት ኢስቲጅማር ማድረግ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ወይ ነጃሳ ስለሆነ ነው። ወይም የጂኖች ምግብ ስለሆነ ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

