አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ!
ከአቡል ዐባስ ዐብደላህ ቢን ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ቀን ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ኋላ ነበርኩ። እንዲህም አሉኝ: "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜ…

