አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁን) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን!
ከዒርባድ ቢን ሳሪያህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህ…

