የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።
ከአቢ ቡርዳህ ቢን አቢ ሙሳ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አቡ ሙሳ ከባድ ህመምን ታመመና ራሱን ሳተ። ጭንቅላቱ ሚስቱ ታፋ ላይ ነበር። (ስታለቅስና ስትገጥም) በርሷ ላይ አንዳችም መልስ መስጠት አልቻለም ነበር። የነቃ ጊዜ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሰው እኔም የጠራሁ ነኝ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸ…

