አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜ ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ጥርጣሬውን ይጣልና እርግጠኛ በሆነበት ላይ ይገንባ። ከዛም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይውረድ።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜ ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ጥርጣሬውን ይጣልና እርግጠኛ በሆነበት ላይ ይገንባ። ከዛም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይውረድ። አምስት ከሰገደ ሁለቱ ሱጁዶች ሶላቱን ጥን…

