ከዑክል ወይም ከዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጡ። መዲና ስላልተስማማቸው ሆዳቸውን ታመሙ።
ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከዑክል ወይም ከዑረይና ጎሳ የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ዘንድ መጡ። መዲና ስላልተስማማቸው ሆዳቸውን ታመሙ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወተት ወዳላቸው ግመሎች በመሄድ ከሽንታቸውና ከወተታቸው እንዲጠጡ አዘዟቸው። የተሻላቸውም ጊዜ የነቢዩን ሶለሏሁ…

