‹ብር በወርቅ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ስንዴ በስንዴ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ገብስ በገብስ መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው፤ ተምር በተምር መለዋወጥ እጅ በእጅ ካልሆነ በቀር አራጣ ነው።›
ከማሊክ ቢን አውስ ቢን ሐደሣን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዲርሃም የሚመነዝርልኝ እያልኩኝ ተዘዋወርኩኝ። ጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ እያለ እንዲህ አለኝ: "ወርቅህን አሳየንና ከዚያም ተመልሰህ ና! አገልጋያችን የመጣ ጊዜ ገንዘብህን እንሰጥሃለን።" በዚህ ጊዜ ዑመር ቢን ኸጧብ እንዲህ አለ: "በፍፁም! በአላህ እምላለሁ! ወይ አሁን ብሩን ትሰጠ…

