HadeethEnc · 1.23.0
ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ (ቁል ሁወሏሁ አሐድ) የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «አንድ ሰውዬ የሆነ ሰው {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን እየደጋገመ ሲያነብ ሰማ። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ነገሩን በሚያቃልል ሁኔታ ይህንን አወሳላቸው። የአላህም መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ (ቁል ሁወሏሁ አሐድ) የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።»
02
Explanation
አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: አንድ ሰውዬ ሌላ ሰው የ{ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን ምዕራፍ ሲያነብ ሰማ። ምሽቱን ሁሉ ሌላ ምዕራፍ ሳይጨምር እርሷን ብቻ ነበር እየደጋገመ የሚያነበው። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ይህንን አወሳላቸው። የጠያቂው አነጋገርም ምዕራፏን ያሳነሳት ይመስላል። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አፅንዖት ለመስጠት በመማል "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።
03
Benefits
የኢኽላስ ምዕራፍ ትሩፋትን እንረዳለን። እርሷም የቁርአንን ሲሶ የምትስተካከል መሆኗ፤
የለይል ሶላት ሲሰገድ ጥቂት አንቀጾችን በመቅራትና እነርሱን በመደጋገም መስገድ እንደሚፈቀድ፤ ይህንንም አሳንሶ ማየት እንደማይገባ እንረዳለን።
ማዚሪይ እንዲህ ብለዋል: «በሐዲሡ ለማለት የተፈለገውን በማስመልከት "ቁርአን ሶስት ክፍሎች አሉት። እነርሱም: ታሪክ፣ ህግጋትና የአላህ ባህሪያት ናቸው። {ቁል ሁወሏሁ አሐድ} የአላህን ባህሪ ብቻ የምታወሳ ናት። ስለዚህ ከሶስቱ ክፍሎች አንዱ ክፍል ናት ማለት ነው።" ተብሏል። ይህቺን ምዕራፍ ማንበብ የሚያስገኘው ምንዳ ሲነባበር የቁርአን ሲሶ ሲነበብ ሳይነባበር የሚያስገኘውን ያህል ይሆናል ማለት ነውም ተብሏል።»

Attribution
[ቡኻሪ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares