HadeethEnc · 1.23.0
የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ "የመጽሐፉ ባለቤቶች ለሙስሊሞች ተውራትን በይብራይስጠኛ እያነበቡ ወደ ዐረብኛ ይተረጉሟት ነበር። የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ። [አልበቀራህ: 136]"
02
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የመጽሐፍ ባለቤቶች ከመጽሐፎቻቸው በሚያወሩት ነገር ከመሸወድ ኡመታቸውን አስጠነቀቁ። ይህም በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ዘመን አይሁዶች ተውራትን በይብራይስጠኛ ቋንቋ (የአይሁዶች ቋንቋ ነው) እያነበቡ ወደ ዐረብኛ ይተረጉሙት ነበር። ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ "የመጽሐፍ ባለቤቶችን አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም" ይህ ግን እውነተኝነቱ ከውሸቱ ባልታወቀበት ጉዳይ ነው። ይህንንም ያሉበት አላህ ወደኛ በወረደው ቁርኣንና ወደነርሱ በወረደው መጽሐፍ እንድናምን ስላዘዘን ነው። ነገር ግን እነሱ ከነዚህ መጽሐፎቻቸው እያጣቀሱ የሚተርኩትን ጉዳዮች በሸሪዐችን እውነተኛውን ከውሸተኛው የሚገልፅልን ስላልተቀመጠ ጤነኛውን ከበሽተኛው ለይተን የምናውቅበት መንገድ የለም። ስለዚህ ፍርድ ከመስጠት እንታቀባለን። መጽሐፉን በመበረዛቸው ላይ እንዳንጋራቸው አናምናቸውም። አላህ እንድናምነው ያዘዘን የሆነን ትክክለኛ ነገር አውርተው ያወገዘ ሰው እንዳንሆንም አናስተባብላቸውም። ስለዚህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ እንድንል አዘዙን። {"በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሓቅም ወደ ያዕቆብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን" በሉ።} [አልበቀራህ: 136]
03
Benefits
የመጽሐፍ ባለቤቶች የተናገሯቸው ጉዳዮች ሶስት ክፍሎች ናቸው። አንዱ ክፍል: ቁርኣንና ሐዲሥን የሚገጥም የሆነ ነው ይህም እናምንበታለን። ሁለተኛው ክፍል: ቁርኣንና ሐዲሥን የሚቃረን ሲሆን ይህም ጥመትና የሚስተባበል ነው። ሦስተኛው ክፍል: በቁርኣንም ሆነ በሐዲሥ ውስጥ እውነተኝነቱንም ስህተቱንም የሚጠቁም አልተገለፀም። ይህ ይወራል ነገር ግን አይታመንበትምም አይስተባበልም።
Attribution
[ቡኻሪ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

