HadeethEnc · 1.23.0
በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐብደሏህ ቢን ዓምር (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "በቃል ኪዳን ስር ያለን (ሙዓሀድን) የገደለ ሰው የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታዋ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት በኋላ ነው።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙዓሀድን በገደለ ሰው ላይ ያለበትን ከባድ ዛቻ ገለፁ። ሙዓሀድ ማለት ከከሀዲያን መካከል በቃል ኪዳንና በደህንነት ከለላ ወደ ኢስላም ሀገር የገባ ነው። እሱን የገደለ የጀነትን ሽታ አያሸትም። የጀነት ሽታ የሚገኘው አርባ አመት ከሚያስኬድ ርቀት ነው።
03
Benefits
ከከሀዲያን መካከል "ሙዓሀድን" ፣ "ዚሚይን" እና "ሙስተእመንን" መግደል ክልክልና ከትላልቅ ወንጀል የሚመደብም ነው።
"ሙዓሀድ" ማለት: ከከሀዲያን መካከል በሀገሩ እየኖረ ሙስሊሞችን ላይዋጋ እነሱም ላይዋጉት ከሙስሊሞች ጋር ቃል ኪዳን የተጋባ ነው። "ዚሚይ" ማለት: በሙስሊሞች ሀገር እንደሀገሩ እየኖረ ግብር የሚከፍል ነው። "ሙስተእመን" ማለት ደግሞ ለተወሰነ ወቅት በቃል ኪዳንና ደህንነት ከለላ ወደ ሙስሊሞች ሀገር የገባ ሰው ነው።
ከሙስሊሞች ውጪ ካሉ ጋር ቃል ኪዳንን ማፍረስ መከልከሉን እንረዳለን።

Attribution
[ቡኻሪ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares