HadeethEnc · 1.23.0
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። እጅግ በጣም ቸር የሚሆኑትም ጂብሪል በሚያገኛቸው ወቅት በረመዷን ነበር። በረመዷን ውስጥም በየሁሉም ምሽት ያገኛቸውና ቁርአን ያስተምራቸው ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአውሎ ንፋስም የበለጠ በመልካም ነገር ላይ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰዎች ሁሉ እጅግ በጣም ቸር ነበሩ። ለሚገባው የሚገባውን በመስጠት ቸርነታቸው የሚበዛውም በረመዷን ወር ነበር። የቸርነታቸው መጨመር ምክንያትም ሁለት ነገሮች ናቸው:
የመጀመሪያው: ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም ማግኘታቸው ሲሆን፤
ሌላኛው ደግሞ: ቁርአንን መማማራቸው ነው። ማለትም ከቀልባቸው በሽምደዳ መቅራታቸው ማለት ነው።
ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም በርሳቸው ላይ የወረደውን ቁርአን ባጠቃላይ ያስተምራቸዋል። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ ቸር፣ አብዝቶ ሰጪ፣ መልካም ተግባሪና አላህ በዝናብና በእዝነት ከሚልካት መልካም ንፋስ የበለጠ ለፍጡራን ፈጥኖ ደራሽ ነበሩ።

03
Benefits
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቸርነት፣ የደግነታቸው ስፋት መገለፁ። በተለይ በረመዷን ወር። ይህም ወሩ የአምልኮ ወርና የመልካም መሸመቻ ወር ስለሆነ ነው።
በሁሉም ወቅት ቸር በመሆን ላይ መነሳሳቱንና በረመዷን ወር ደግሞ ቸርነትን መጨመር እንደሚገባ እንረዳለን።
በረመዷን ወር አብዝቶ መለገስ፣ መስጠት፣ በጎ መስራትና ቁርአን መቅራት እንደሚገባ እንረዳለን።
እውቀትን ለመሸምደድ ከሚረዱ ሰበቦች አንዱ ከእውቀት ፈላጊዎችና ዑለሞች ጋር መማማሩ ነው።
በሁሉም ወቅት ቸር በመሆን ላይ መነሳሳቱንና በረመዷን ወር ደግሞ ቸርነትን መጨመር እንደሚገባ እንረዳለን።
በረመዷን ወር አብዝቶ መለገስ፣ መስጠት፣ በጎ መስራትና ቁርአን መቅራት እንደሚገባ እንረዳለን።
እውቀትን ለመሸምደድ ከሚረዱ ሰበቦች አንዱ ከእውቀት ፈላጊዎችና ዑለሞች ጋር መማማሩ ነው።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares