አዋቂ (ዐሊም) አላህን አብዝቶ ከሚገዛ ባሪያ (ከዐቢድ) ጋር ያለው ልዩነት እኔ ከናንተ መካከል ከዝቅተኛው ሰው ጋር እንዳለኝ ልዩነት ነው።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
አቡ ኡማመተል ባሂሊይ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «ለአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለሁለት ሰዎች ተነገራቸው። አንደኛው አላህን አብዝቶ የሚገዛ ሲሆን ሌላኛው ዓሊም (አዋቂ) ነው። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "አዋቂ (ዐሊም) አላህን አብዝቶ ከሚገዛ ባሪያ (ከዐቢድ) ጋር ያለው ልዩነት እኔ ከናንተ መካከል ከዝቅተኛው ሰው ጋር እንዳለኝ ልዩነት ነው።" ቀጥለው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ "አላህ፣ መልአክቶቹና፣ ጓድጓዷ ውስጥ ያለች ጉንዳን፣ ዓሳ እንኳን ሳትቀር የሰማያትና የምድር ነዋሪዎች መልካም በሚያስተምሩ ላይ ሶላት ያወርዳሉ።"»
Explanation
ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡ "የሸሪዓን እውቀቶች አውቆ በእውቀቱ ከመስራት አልፎ የሚያስተምር ሰው ማወቅ ያለበትን ግዴታዎች አውቆ ራሱን ለአምልኮ ብቻ ነፃ ካደረገ ሰው ጋር ያለው ልዩነት ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሶሓቦች ሁሉ ዝቅተኛ ከሆነው ጋር እንዳላቸው ልዩነትና ደረጃ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የዚህን ምክንያት እንዲህ በማለት ገለፁ። አላህ ሱብሓነሁ፣ የዐርሽ ተሸካሚ የሆኑ መልአክቶቹ፣ የተቀሩትም ሰማይ ውስጥ የሚኖሩ መልአክቶች፣ በምድር የሚኖሩ ሰዉም ጂንም አጠቃላይ እንስሶችም፣ ጉንዳን እንኳን ከምድር በታች ባለው ቤቷ ሳይቀር፣ አሳና የባህር እንስሶችም ሳይቀሩ የየብሱም ይሁን የባህሩ እንስሶች ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ መዳኛቸውና መድህናቸው የሆነውን መልካም ነገርና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለሚያስተምር ሰው ዱዓ ያደርጋሉ።
Benefits
እውቀትን የተማሩና ባወቁት በመስራትና ወዳወቁት በመጣራት ላይ የእውቀትን ሐቅ የተወጡ ዑለማዎችን ደረጃና ልቅና እንረዳለን።
ዑለማዎችንና እውቀት ፈላጊዎችን በማክበርና ለነርሱ ዱዓ በማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሰዎችን መልካም ነገር በማስተማር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም የደስታቸውና የመዳናቸው ምክንያት ነውና።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

