HadeethEnc · 1.23.0
አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር እስካልሰሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ ይቅር ብሏቸዋል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር እስካልሰሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ ይቅር ብሏቸዋል።"
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ወንጀልነቱን ስላነሳና ይቅር ስላለ አንድ ሙስሊም በውስጡ አስቦ ለተወው መጥፎ ነገር እስካልሰራበት ወይም እስካልተናገረው ድረስ እንደማይያዝበት ተናገሩ። የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡመት በአይምሯቸው በሚገኝ፣ ልባቸው ላይ ሳይረጋጋና ሳይፀናበት ውስጣቸው ላይ በመጣ መጥፎ ነገር አይያዙም። እንደኩራት፣ መንጠባረርና ንፍቅና ቀልቡ ላይ ከፀናበት፣ በአካሉ ከተገበረ ወይም በምላሱ ከተናገረ ግን ይያዝበታል።
03
Benefits
አላህ ተባረከ ወተዓላ በነፍስ ላይ የምትመጣንና ሰውዬው በውስጡ የሚናገራትንና ውል የምትልበትን አስተሳሰብና ሹክሹክታ ይቅር ብሏልም አልፏልም።
አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት ቢያስብና በውስጡ ውል ቢልበትም ነገር ግን ካልተናገረና ካልፃፈው ፍቺ ተደርጎ አይቆጠርበትም።
በውስጥ የሚወራ ወሬ ምንም ያህል ቢገዝፍ በውስጡ እስካልፀና፣ በርሱ እስካልሰራ ወይም እስካልተናገረ ድረስ አይያዝበትም።
የሙሐመድ ኡመት (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከኛ በፊት ከነበሩት ህዝቦች በተቃራኒ ከራሳቸው ጋር በውስጥ በማውራታቸው ባለመያዝ የተለዩ መሆናቸው ደረጃቸው የላቀ መሆኑን ያስረዳናል።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares