HadeethEnc · 1.23.0
ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"
02
Explanation
ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ።
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"
03
Benefits
አንድ አማኝ ከፀያፍ ንግግርና ከመጥፎ ተግባር ሊርቅ እንደሚገባው እንረዳለን።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ምሉዕ መሆኑንና ከሳቸው መልካም ስራና ምርጥ ንግግር እንጂ ሌላ እንደማይመነጭ እንረዳለን።
መልካም ስነምግባር የሽቅድድም መድረክ መሆኑን እንረዳለን። የቀደመም ምርጥ አማኝና ኢማኑ የሞላ ይሆናል።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ምሉዕ መሆኑንና ከሳቸው መልካም ስራና ምርጥ ንግግር እንጂ ሌላ እንደማይመነጭ እንረዳለን።
መልካም ስነምግባር የሽቅድድም መድረክ መሆኑን እንረዳለን። የቀደመም ምርጥ አማኝና ኢማኑ የሞላ ይሆናል።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares