HadeethEnc · 1.23.0
'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች: "የአላህ መልክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'አንድ ሙእሚን በመልካም ስነምግባሩ የፆመኛና (የሌሊት) ሰጋጅን ደረጃ ያገኛል።'"
02
Explanation
መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው ቀኑን በመፆምና ሌሊቱን በመቆም የዘወተረ ሰውን ደረጃ እንደሚደርስ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ። መልካም ስነምግባር ሲጠቀለል: መልካምን መለገስ፣ ንግግርን ማሳመር፣ ፊትን መፍታት፣ ሰውን ከመጉዳት መቆጠብና የነሱን ክፋት መቻል ነው።
03
Benefits
ኢስላም ስነምግባርን በማጥራትና በማሟላት ላይ ትልቅ ትኩረት መቸሩን እንረዳለን።
አንድ ሰው በመልካም ስነምግባሩ ቀን ምንም ሳያፈጥር የሚፆምና ምንም ሳይደክም ሌሊቱን የሚቆም ሰው ደረጃ ላይ መድረሱ የመልካም ስነምግባርን ትሩፋት ያስረዳናል።
ቀኑን መፆምና ሌሊቱን መቆም ለነፍስ የሚከብዱ ትልልቅ ስራዎች ናቸው። መልካም ስነምግባርን የተላበሰ ሰው የነርሱን ደረጃ የደረሰው ነፍሱን በመልካም መስተጋብር ላይ ስለታገለ ነው።

Attribution
[አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares