በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»
Explanation
Benefits
አንድ ዱዓ አድራጊ የዱዓን ስነስርዓቶች ካሟላ፣ ዱዓ ለማድረግ በላጩን ወቅትና ስፍራ ካለመ፣ አላህን ከማመፅ ከራቀ፣ ነፍሱ አምታታችና አጠራጣሪ ነገር ውስጥ እንዳትገባ ከተጠነቀቀ፣ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ካሳመረ በአላህ ፈቃድ ዱዓው ተቀባይነት ለማግኘት የተገባ ነው።
ስለዱዓ ተቀባይነት ማግኘት አልሙናዊ እንዲህ ብለዋል: «ማለትም የዱዓ መስፈርቶችን፣ ማዕዘናቶችንና ስነስርዓቶች ካሟላ በኋላ ከለመነው እንጂ ያጓደለው ነገር ካለ በመስተጓጎሉ ከነፍሱ በቀር ማንንም አይውቀስ።»
የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት: ወይ የለመነው በፍጥነት ትገኝለታለች ወይም በለመነው አምሳያ ጉዳት ዞር ይደረግለታል ወይም በመጪው አለም ለርሱ ድልብ ይደረግለታል። ይህም እንደአላህ ጥበብና እዝነት የሚወሰን ነው።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

