ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።"
Explanation
Benefits
ምንዳ በስራው አምሳያ ነው የሚሰጠው። ዝምድናውን በበጎና መልካምነት የቀጠለ ሰውን አላህም እድሜውና ሲሳዩን ይቀጥልለታል።
ዝምድናን መቀጠል ለሲሳይ መስፋትና መዘርጋት እንዲሁም ለእድሜ መርዘም ምክንያት ነው። ምንም እንኳ የመሞቻ ቀኑና ሲሳዩ የተወሰነ ቢሆንም ባለው ሲሳይና እድሜ በረከት ይሰፍንበታል። የተሰጠውን እድሜ ሌላው ከሚጠቀምበት በላይ ይጠቀምበታል። በርግጥ የሲሳይና እድሜ መጨመሩ እውነተኛ መጨመር ነውም ተብሏል። አላህ እጅግ አዋቂ ነው!
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

