HadeethEnc · 1.23.0
ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "መንገድ ተቋርጦብኛልና የምጓጓዝበት እንስሳ ይስጡኝ?" አላቸው። እሳቸውም "የለኝም!" አሉት። ሌላ ሰውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ መጓጓዣ የሚሰጠውን እጠቁመዋለሁ!" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።" አሉ።
02
Explanation
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "እኔ ግመሌ ስለጠፋች የሚያደርሰኝን አንድ መጓጓዣ ይስጡኝ!" አላቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እሳቸው የሚሰጡት ምንም ነገር እንደሌለ ነገሩት። እሳቸው ዘንድ የነበረ አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ የሚሰጠውን ሰው እጠቁመዋለሁ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምፅዋት ፈላጊን ለሚመፀውተው አካል በመጠቆሙ ምክንያት ጠቋሚው ከሚመፀውተው ሰው ጋር በአጅር እንደሚጋራ ተናገሩ።
03
Benefits
ወደ መልካም ነገር መጠቆም መበረታታቱን እንረዳለን።
መልካም በመፈፀም ላይ መቀስቀስ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እርስ በርስ እንዲተባበሩና እንዲዋሃዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
የአላህ ችሮታ ሰፊ መሆኑን እንረዳለን።
ሀዲሱ ሁሉን የሚያካትት መርህ ስለሆነ በውስጡ ሁሉም መልካም ስራዎች የሚገቡ መሆኑን እንረዳለን።
የሰው ልጅ የጠያቂን ፍላጎት ማሳካት ካልተመቻቸለት ለጠያቂው የሚያሳካለትን ሌላ አካል መጠቆም እንዳለበት እንረዳለን።

Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares