HadeethEnc · 1.23.0
ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ: "ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"
02
Explanation
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካምን ከመፈፀም እንዳናሳንስ አነሳሱን። ከነዚህ መካከልም ከሙስሊም ጋር በሚገናኝ ወቅት በፈገግታ ፊትን መፍታት ይጠቀሳል። አንድ ሙስሊም ይህን በመፈፀሙ ምክንያት ሙስሊም ወንድሙን ማዝናናትና በውስጡ ደስታን መጨመር ስለሚያመጣ በዚህ ላይ ሊጥር ይገባል።
03
Benefits
በአማኞች መካከል መዋደድ፣ ሲገናኙ ፈገግ ማለትና ማበሰር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
ሸሪዓ ለሙስሊሞች በሚጠቅምና ህብረታቸውን አንድ በሚያደርግ ነገር ሁሉ መምጣቱ የዚህ ሸሪዓን ምሉዕነትና ጠቅላይነት ያስረዳናል።
ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
በሙስሊሞች መካከል አንድነትን ስለሚያረጋግጥ በሙስሊሞች ላይ ደስታን መጨመር ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።
ሸሪዓ ለሙስሊሞች በሚጠቅምና ህብረታቸውን አንድ በሚያደርግ ነገር ሁሉ መምጣቱ የዚህ ሸሪዓን ምሉዕነትና ጠቅላይነት ያስረዳናል።
ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱን እንረዳለን።
በሙስሊሞች መካከል አንድነትን ስለሚያረጋግጥ በሙስሊሞች ላይ ደስታን መጨመር ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares