HadeethEnc · 1.23.0
አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከመዕቂል ቢን የሳር አልሙዘኒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: እኔ የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።"
02
Explanation
እያንዳንዱ አላህ በሰዎች ላይ ተጠያቂና ሀላፊ ያደረገው ሁሉ እንደመሪነት ጠቅላይ ሀላፊነትን የሚያስተዳድርም ይሁን ወይም በቤቱ ሀላፊ እንደሆነ ወንድና በቤቷ ሀላፊ እንደሆነች ሴት ውስን ሀላፊነትም ይሁን የሀላፊነት ግዴታውን ካጓደለ፣ ቅን ሳይሆን ካጭበረበረና ዲናዊና ዓለማዊ ግዴታውን ካጠፋ ለከባድ ቅጣት እንደተገባ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።
03
Benefits
ይህ ዛቻ በጠቅላይ መሪውና ሚኒስትሮቹ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን አላህ በሀላፊነት የሾመውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።
በአንዳች የሙስሊሞች ጉዳይ ላይ የተሾመ ሰው ያለበት ግዴታ ለነሱ ቅን መሆን፣ አደራውን በመወጣት ላይ መታገልና ማጭበርበርን መጠንቀቅ ነው።
ጠቅላይም ይሁን ውስን፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሀላፊነት ላይ የተሾመ ሁሉ ተጠያቂነቱ ትልቅ መሆኑን እንረዳለን።
በአንዳች የሙስሊሞች ጉዳይ ላይ የተሾመ ሰው ያለበት ግዴታ ለነሱ ቅን መሆን፣ አደራውን በመወጣት ላይ መታገልና ማጭበርበርን መጠንቀቅ ነው።
ጠቅላይም ይሁን ውስን፣ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሀላፊነት ላይ የተሾመ ሁሉ ተጠያቂነቱ ትልቅ መሆኑን እንረዳለን።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

