HadeethEnc · 1.23.0
አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቴ ውስጥ ይህንን ሲሉ ሰምቻለሁ: "አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።"
02
Explanation
የሙስሊሞች ጉዳዮች ውስጥ በየትኛውም ትንሽም ይሁን ትልቅ ሹመት ፣ አጠቃላይም ይሁን ቁንፅል ሹመትን የተሾመ ከዚያም ለሙስሊሞች ሳይራራ ችግርን በነርሱ ላይ የሚያባብስባቸው የሆነን ሰው ሁሉ ላይ አላህ በሰራው ስራ ተመሳሳይ እሱንም ለችግር እንዲዳርገው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አደረጉበት።
ለነርሱ የራራና ጉዳዮቻቸውን ባቀለለ ላይም አላህ ለርሱ እንዲራራና ጉዳዮቹን እንዲያገራለት ዱዓ አደረጉለት።
ለነርሱ የራራና ጉዳዮቻቸውን ባቀለለ ላይም አላህ ለርሱ እንዲራራና ጉዳዮቹን እንዲያገራለት ዱዓ አደረጉለት።
03
Benefits
ከሙስሊሞች ጉዳዮች መካከል አንድ ነገር ላይ የተሾመ ሰው በቻለው መጠን ለነርሱ መራራት ግዴታው መሆኑን እንረዳለን።
ምንዳ የሚሰጠን በስራችን አይነት መሆኑን እንረዳለን።
የመራራትና የሀይለኝነት መለኪያ ሚዛኑ ቁርአንና ሐዲሥን ባልተፃረረ መልኩ መሆኑን እንረዳለን።
ምንዳ የሚሰጠን በስራችን አይነት መሆኑን እንረዳለን።
የመራራትና የሀይለኝነት መለኪያ ሚዛኑ ቁርአንና ሐዲሥን ባልተፃረረ መልኩ መሆኑን እንረዳለን።
Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

