ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ይሉ ነበር።» ትርጉሙም "ጌታችን ሆይ! ከምስጋና ጋር ጥራት የተገባህ ነህ! አላህ ሆይ! ማረኝ።" ማለት ነው። ከእናታችን ዓኢሻ እንደተላለፈው እንዲህም ብላለች: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቁርአን ላይ የመጣውን ትእዛዝ ወደ ተግባር ለመለወጥ በሩኩዓቸውና በሱጁዳቸው ወቅት "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ" ማለትን ያበዙ ነበር።
Explanation
Benefits
በእድሜ መጨረሻ ወቅት ምህረት መጠየቅ እንደሚገባ እንረዳለን። ልክ እንደዚሁ አምልኮ ውስጥ የተከሰቱ ጉድለቶች እንዲሟሉም አምልኮዎችን (በተለይም ሶላትን) ምህረትን በመጠየቅ እንድናጠናቅቅ ያስገነዝባል።
ዱዓ ተቀባይነት እንዲያገኝ ወደ አላህ ከምንቃረብባቸው ነገሮች መካከል ያማረው መመስገኛዎቹን ማውሳትና እርሱን ከጉድለቶችና ነውሮች የጠራና የፀዳ መሆኑን ማውሳት ነው።
አላህን ምህረት መጠየቅ ያለው ትሩፋትና በሁሉም ሁኔታዎች ተፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አምልኮ የተሟላ መሆኑንና የአላህንም ትእዛዝ በተሟላ መልኩ መተግበራቸውን እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

