HadeethEnc · 1.23.0
ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው በዲናዊ፣ በዱንያዊ፣ ለራሱ በሚሰራቸው፣ ከሌሎች ጋርም ባለው ጉዳዮች ለስላሳነትን ያልተገጠመ (ያልታደለ) ሰው በርግጥም መልካምን ሁሉ እንደተነፈገ ተናገሩ።
03
Benefits
የለስላሳነት ትሩፋትን፣ እርሱን በመላበስ መነሳሳቱንና ድርቅና መወገዙን እንረዳለን።
በለስላሳነት የሁለቱም ሀገር ስርአት መስተካከልና የሁለቱም ሀገር ጉዳዮች መቅለል ሲገኝ በድርቅና ግን የዚህ ተቃራኒ ነው የሚገኘው።
ለስላሳነት ከመልካም ስነምግባርና ከሰላማዊነት የሚመነጭ ሲሆን ድርቅና ደግሞ ከቁጡነትና ከመጥፎ ስነምግባር የሚመነጭ ነው። ለዚህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለስላሳነትን አወደሱም እጅግም አሞካሹት።
ሱፍያን አሥሠውሪይ አላህ ይዘንላቸውና ለባልደረቦቻቸው "ለስላሳነት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሉ። ቀጥለውም "እርሱም ሁሉንም በቦታቸው ማስቀመጥ ነው። ብርቱነትን በቦታው፣ ልስላሴን በቦታው፣ ሰይፍን በቦታው፣ አለንጋን በቦታው ማስቀመጥ ነው።" አሉ።

Attribution
[ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares