HadeethEnc · 1.23.0
ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ጨረቃን ባያችሁ ጊዜ ፁሙ! ባያችሁት ጊዜ ፆም ፍቱ! ከተጋረደባችሁ ደሞ ልኩን ገምቱለት።"»
02
Explanation
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የረመዿን ወር መግቢያና መውጫን ምልክት ገለፁ። እንዲህ አሉ: የረመዿንን ጨረቃ ያያችሁ ጊዜ ፁሙ። በናንተና በጨረቃው መካከል ደመና ከገባና ከጋረዳችሁ ደሞ የሸዕባንን ወር ሰላሳ አድርጋችሁ ቁጠሩ። የሸዋልን ጨረቃ ያያችሁ ጊዜ ፆም ፍቱ። በናንተና በጨረቃው መካከል ደመና ከገባና ከጋረዳችሁ የረመዿንን ወር ሰላሳ አድርጋችሁ ቁጠሩ።
03
Benefits
የወር መግባት ለማረጋገጥ የምንደገፈው በሂሳብ ሳይሆን ጨረቃን በማየት ነው።
የረመዿን ወር መግባቱን ጨረቃን ሳያዩ በሂሳብ ላይ ብቻ በመመርኮዝ መጾም ግዴታ እንዳልሆነ ኢብኑል ሙንዚር የዑለሞችን ሙሉ ስምምነት ጠቅሰዋል።
የረመዿንን ጨረቃ ከማየት ደመና ወይም መሰል ነገር ከጋረደ ሸዕባንን ሰላሳ ቀን መሙላት ግዴታ ነው።
የጨረቃ ወር ሀያ ዘጠኝ ቀን ወይም ሰላሳ ቀን ብቻ ነው የሚሆነው።
ደመና ወይም መሰል ነገር የሸዋልን ጨረቃ እንዳናይ ከጋረደ ረመዿንን ሰላሳ ቀን መሙላት ግዴታ ነው።
በፆም ጉዳይ የሙስሊሞችን ሁኔታ የሚከታተል በሌለበት ስፍራ የሚኖር ወይም ይህንን ችላ በሚሉ ሰዎች ባሉበት ስፍራ የሚኖር ከሆነ ይህንን በራሱ ወይም በሚያምነው ሰው በማየት የሚያረጋግጥበትን ነገር መከታተልና መጠባበቅ ይገባል። በዛም ላይ በመመርኮዝ ይጾማልም ይፈታልም።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares