HadeethEnc · 1.23.0
ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም ለረመዷን ጥንቃቄ ብሎ ረመዷን ከመግባቱ ከአንድ ቀን ወይም ከሁለት ቀን በፊት መጾምን ከለከሉ። ምክንያቱም የረመዷን ጾም ግዴታነት የተያያዘው ጨረቃን ከመመልከት ጋር ነውና። ስለዚህ መጨናነቅ አያስፈልግም። ነገር ግን አንድ ቀን እየጾመ አንድ ቀን የመብላት ልምድ ያለው ወይም ሰኞና ሀሙስ የመጾም ልምድ ያለው አይነቱ ሰው ከሆነ ከዚህ ልምዱ ጋር ከገጠመ መጾም ይችላል። ይህም በምንም መልኩ የረመዷን አቀባበል ስላልሆነ ነው። እንደስለትና የቀዷእ (ያመለጠን ግዴታ ፆም ማካካሻ) ጾም የመሰሉ ግዴታ ጾሞች እዚህ (የተፈቀደው) ውስጥ ይካተታሉ።
03
Benefits
እራስን ማስጨነቅ መከልከሉንና ያለምንም ጭማሪና ማጓደል በተደነገገው መልኩ አምልኮ በመፈፀም ላይ መጠባበቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
የዚህ ጥበብ ምክንያትም -አላህ ይበልጡን ያውቃል- ግዴታ አምልኮዎችን ከሱንና (ግዴታ ካልሆኑ) አምልኮዎች ለመለየት፤ ለረመዷን በንቃትና በተነሳሽነት እንዲዘጋጅ እና ጾም የዚህ ታላቅ ወር መገለጫ እንዲሆን ሲባል ነው።
የዚህ ጥበብ ምክንያትም -አላህ ይበልጡን ያውቃል- ግዴታ አምልኮዎችን ከሱንና (ግዴታ ካልሆኑ) አምልኮዎች ለመለየት፤ ለረመዷን በንቃትና በተነሳሽነት እንዲዘጋጅ እና ጾም የዚህ ታላቅ ወር መገለጫ እንዲሆን ሲባል ነው።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

