HadeethEnc · 1.23.0
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።»
02
Explanation
አቡሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሳታገባና ወንዶች ጋር ሳትኗኗር በቤቷ ተሸሽጋ ከምትኖር ልጃገረድ ሴት የበለጠ አይነአፋር እንደነበሩ ተናገረ። እጅግ አይነአፋር ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ነገር የጠሉ ጊዜ ፊታቸው ይለዋወጣል እንጂ አይናገሩም። ይልቁኑም ባልደረቦቻቸው ፊታቸውን በመመልከት ያንን ነገር መጥላታቸውን ይረዳሉ።
03
Benefits
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተላበሱት አይነአፋርነት መገለፁ። ይህ ባህሪም ትልቅ ስነምግባር ነው።
የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይነአፋርነት የአላህ ክልከላ እስካልተደፈረ ድረስ ነው። የአላህ ክልከላ ከተደፈረ ግን ይቆጡ፣ ባልደረቦቻቸውንም የሚያዙና የሚከለክሉ ነበሩ።
የአይነአፋርነትን ባህሪ በመላበስ መነሳሳቱን እንረዳለን። አይነአፋርነት ነፍስ መልካም ተግባር እንድትሰራና ፀያፍን እንድትተው ይገፋፋታልና።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares