HadeethEnc · 1.23.0
ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰው ልጅ ፍፁም ጓደኛውንና ባልደረባውን በልማዱና ኑሮው እንደሚመሳሰል፤ ጓደኝነትም በስነምግባር፣ በባህሪና የኑሮ ዘይቤ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ገለፁ። ለዚህም ጥሩ ጓደኛ ወደ ኢማን፣ ቅናቻና መልካም ነገር ይጠቁማልም ለባልደረባውም አጋዥ ይሆናልና ጓደኛ አመራረጣችንን እንድናሳምር ጠቆሙ።
03
Benefits
መልካሞችን በመወዳጀትና በመምረጥ መታዘዙን፤ መጥፎዎችን መወዳጀት ደግሞ መከልከሉን እንረዳለን።
ከዘመድ ይልቅ ጓደኛን ብቻ ለይተው መጥቀሳቸው ጓደኛ አንተ ራስህ የምትመርጠው ስለሆነ፤ ወንድምና ቅርብ ዘመድ ግን አንተ ምንም ምርጫ ስለሌለህ ነው።
ጓደኛን መያዝ የግድ ጥናት ካደረግክ በኋላ መሆን አለበት።
አንድ ሰው አማኞችን በመወዳጀት ዲኑን እንደሚያጠነክርና አመፀኞችን በመወዳጀት ደግሞ እንደሚያደክመው እንረዳለን።
ከዘመድ ይልቅ ጓደኛን ብቻ ለይተው መጥቀሳቸው ጓደኛ አንተ ራስህ የምትመርጠው ስለሆነ፤ ወንድምና ቅርብ ዘመድ ግን አንተ ምንም ምርጫ ስለሌለህ ነው።
ጓደኛን መያዝ የግድ ጥናት ካደረግክ በኋላ መሆን አለበት።
አንድ ሰው አማኞችን በመወዳጀት ዲኑን እንደሚያጠነክርና አመፀኞችን በመወዳጀት ደግሞ እንደሚያደክመው እንረዳለን።
Attribution
[አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

