HadeethEnc · 1.23.0
ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: «"ከአዳኝ ወይም ከከብት ጠባቂ ውሻ ውጪ የሆነ ውሻን ያሳደገ ሰው በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጦች ይቀነሱበታል።" ሳሊም እንዲህ አለ: አቡ ሁረይራም የእርሻ ባለቤት ነበርና "ወይም የእርሻ ጠባቂ ውሻ ካልሆነ" ይል ነበር።»
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለአደን ወይም ለከብቶችና አዝርዕት ጥበቃ ፈልጎ ካልሆነ በቀር ውሻን ከማሳደግ ከለከሉ። ከነዚህ ውጪ ለሆነ አላማ ያሳደገ ሰውም በየቀኑ ከስራው ሁለት ቂራጥ ምንዳ ይቀነስበታል። ቂራጥ ሲባል የተፈለገው መጠንን የሚያውቀውም አላህ ብቻ ነው።
03
Benefits
አንድ ሙስሊም ከተገደቡለት አላማዎች ውጪ ውሻን ማሳደግ አይፈቀድለትም።
ውሻ ብዙ ጉዳትና ብልሽት ስለሚያስከትል ማሳደጉ የተከለከለ ነው። ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደተረጋገጠው መላእክቶች ውሻ ያለበት ቤት ውስጥ አይገቡም። በተጨማሪም ውሻ ውስጥ ደጋግሞ በውሃና አፈር በማጠብ ካልሆነ በቀር የማይወገድ ከባድ ነጃሳ አለ።
ውሻ ብዙ ጉዳትና ብልሽት ስለሚያስከትል ማሳደጉ የተከለከለ ነው። ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደተረጋገጠው መላእክቶች ውሻ ያለበት ቤት ውስጥ አይገቡም። በተጨማሪም ውሻ ውስጥ ደጋግሞ በውሃና አፈር በማጠብ ካልሆነ በቀር የማይወገድ ከባድ ነጃሳ አለ።
Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares