HadeethEnc · 1.23.0
በሩብ ዲናርና ከዛ በላይ በሚያወጣ (ስርቆት) እጅ ይቆረጣል።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከአማኞች እናት ከዓኢሻህ (ረዲየሏሁ ዓንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "በሩብ ዲናርና ከዛ በላይ በሚያወጣ (ስርቆት) እጅ ይቆረጣል።"»
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአንድ ዲናር ሩብ እና ከዚህ በላይ የሚያወጣን ነገር የሰረቀ ሌባ እጁ እንደሚቆረጥ ገለፁ። ዋጋውም በንፁህ ወርቅ የ 1.06 ግራም ዋጋን ይመዝናል።
03
Benefits
ስርቆት ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ነው።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የሌባን ቅጣት ወስኗል። እርሱም እጁን መቁረጥ ነው። አላህ እንዲህ እንዳለው {ሰራቂውንና ሰራቂይቱንም እጆቻቸውን ቁረጡ።} [አልማኢዳህ:38] የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱናም የሚቆረጥበትን መስፈርቶች አብራርቷል።
ሐዲሡ ውስጥ እጅ በማለት የተፈለገው መዳፍን ሲሆን በርሱና በክንዱ መካከል ከሚለየው አጥንት መቁረጥ ነው።
የሌባን እጅ የመቁረጡ ጥበብ የሰዎችን ገንዘብ መጠበቅና ሌሎችን ወሰን አላፊዎች ማስጠንቀቅ ነው።
ዲናር ማለት አንድ ሚሥቃል ወርቅ ነው። በዚህ ዘመንም በ24 ካራት ወርቅ (4.25 ግራም) ይመዝናል። የአንድ ዲናር ሩብም አንድ ግራም ከተወሰነ ሚሊ ግራም ይመዝናል።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares